በአዲስ አበባ መንግስት ዝርዝር ነገር እስኪያወጣ ድረስ ታክሲዎች በግማሽ መጫናቸውን እንዲቀጥሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳሰበ።

በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት በተለይም የታክሲ አገልግሎት በግማሽ እንዲጭኑ ተሳፋሪዎች በእጥፍ እንዲከፍሉ መደረጉ ይታወሳል።

ለአምሰት ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ነሀሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም መጠናቀቁን ተከትሎ የተወሰኑ ክልሎች በግማሽ የመጫን አገልግሎቱ መነሳቱን አሳውቀዋል።

ይሁንን በአዲስ አበባ ታክሲዎች የአስቸኳይ አዋጁ መጠናቀቁን ተከትሎ ለምን ወደ ቀድሞው የትራስፖርት አገልግሎት አይመለስም ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮን ጠይቋል።

የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ እንዳሉት ጉዳዩን በተመለከተ በመግለጫ እስከምናሳውቅ ድረስ ታክሲዎች በግማሽ መጫናቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ቢሮው ከደቂቃዎች በኋላ መግለጫ የሚሰጥ በመሆኑ ዝርዝር ነገሮችን ይፋ እናደርጋለን ብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.