ቻይና በአራት የአፍሪካ ሀገራት የጦር ሰፈር ልትገነባ በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗን አሜሪካ አስታወቀች።

የአሜሪካ የመከላከያ ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት ቻይና በአራት አፍሪካ ሀገራት ውስጥ የጦር ሰፈር ለማቋቋም አስባለች ሲል ነው ያስታወቀው፡፡

ቻይና የጦር ሰፈር ልትከፍትባቸው ያሰበቻቸው ሀገራትም ኬንያ፣ ሲሼልስ፣ ታንዛኒያና አንጎላ መሆቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሌሎችም የአፍሪካ ሀገራት በእቅዳቸው እንዳለ የተገለጸ ሲሆን ሀገራቱ ግን እነማን እንደሆኑ ለማወቅ አልተቻለም፡፡

የጦር ሰፈር ይገነባባቸዋል የተባሉት ሀገራት እስካሁን ድረስ ስለ መረጃው የሰጡት አንድም ምላሽ የለም፡፡

ሀገራቱ ስለመረጃው ከመናገር ይቆጠቡ እንጂ የየሀገራቱ ሚዲያዎች ግን በስፋት እየተቀባበሉት ነው የሚገኙት፡፡

ቻይና ከዚህ በፊት በጅቡቲ የጦር ሰፈር እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን ከጅቡቲ በተጨማሪም በአራት ሀገራት ውስጥ የእግረኛ የባህር እንዲሁም የአይር ጦር ሰፈር ልትከፍት እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

የአሜሪካ መንግስትም ይህ መረጃ ይፋ ከሆነ በኃላ የቻይናን እንቅስቃሴ በጥብቅ ተቃውሞታል፡፡

በዚህ የተነሳም ሁለቱ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ የፈጠሩትን እሰጣ ገባ በአፍሪካ ለመድገም የተዘጋጁም ነው የሚመስለው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.