በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት በተለይም የታክሲ አገልግሎት በግማሽ እንዲጭኑ ተሳፋሪዎች በእጥፍ እንዲከፍሉ መደረጉ ይታወሳል።
ለአምስት ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ነሀሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም መጠናቀቁን ተከትሎ ትራንስፖርቱ በተለይም ከመናሀሪያዎች የሚደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ቀድሞ ይዘቱ መመለሱ ተገልጿል።
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አውቶቡሶች ከጷግሜ 1 ቀን 2012 ዓ.ም አንስቶ በወንበር ልክ እና በታሪፉ መሰረት ተሳፋሪዎቻቸውን ማስተናገድ መጀመራቸውን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።
የአማራ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ የአስቸኳይ አዋጁ መነሳቱን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በወንበር ልክ እና በተቀመጠላቸው ታሪፍ ተሳፋሪዎችን እንዲጭኑ ማድረጉ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በበኩሉ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መግለጫ እስከምሰጥ ድረስ ታክሲዎች በግማሽ መጫናችሁን ቀጥሉ ብሏል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በደረሰ አማረ
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም











