የሱዳን መንግሥት እና ታጣቂ ቡድኖች የመጨረሻውን የሰላም ስምምነት የፊታችን ጥቅምት 2 ይፈራማሉ ተባለ፡፡

በሱዳን መንግስት እና በአማፅያን ቡድኖች መካከል የተጀመረው የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ፊርማ የፊታችን ጥቅምት 2 በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ እንደሚካሄድ የድርድሩ ዋና አሸማጋይ አስታውቀዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ጉዳዮች ፕሬዝዳንት አማካሪ እና የሽምግልና ቡድኑ መሪ የሆኑት ቱት ጋትሉክ በቲውተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት በሱዳን መንግስትና አማፅያኑ መካከል ሁለተኛው እና የመጨረሻው የሰላም ስምምነት ፊርማ የፊታችን ጥቅምት 2 ይፈራረማሉ ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ከሱዳን የሽግግር መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ሂደት ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙት የሱዳን ታጣቂ ቡድኖች «የእኩልነት እንቅስቃሴ «JEM» እና ሚኒ ሚናዊ ፤ በምዕራብ እና ሰሜን ዳርፉር የሚገኙ የሱዳን ነጻ አዉጪ «SLA» እንዲሁም በብሉ ናይል እና ኮርዶፋን ግዛት የሚገኙት የሱዳን ነጻ አዉጪ ንቅናቄ የተባሉት መሆናቸዉ ተገልጿል።

እነዚህ ታጣቂ ቡድኖች ከሱዳን መንግስት ጋር ባሳለፍነው ሳምንት መግቢያ ላይ የመጀመሪያውን የሰላም ስምምነት ፊርማ በወሳኝ ነጥቦች ላይ በመግባባት ማኖራቸው ይታወሳል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *