የአሥራት ጋዜጠኞች በዋስትና እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ

አራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሥራት ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ ማስተላለፉን አስራት ሚዲያ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

ፖሊስ በተደጋጋሚ መረጃ አቀርባለሁ በሚል ቀጠሮ እንዲሰጠው ቢጠይቅም በተሰጠው ቆጠሮ አለኝ ያለውን መረጃ ማቅረብ አልቻለም።

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብር፣ ምስጋናው ከፈለኝ እና ዮናታን ሙሉጌታ በእያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *