በሱዳን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡

በሱደን በጣለው ሀይለኛ ዝናብ ምክንያት የተከሰተው ከባድ ጎርፍ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነ ሲሆን 46 ያህል ሰዎች ደግሞ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚድልኢስት ሞኒተር ዘገባ ያሳያል፡፡

ካሳለፍነው ቅዳሜ ጀምሮ የተከሰተው ከባድ ዝናብ እና ጎርፍም 24 ሺ 582 ቤቶችን የወሰደ ሲሆን 40 ሺ 415 ቤቶች ደግሞ በከፊል እንዲፈርሱ አድርጓል ነው የተባለው፡፡

ሱዳን በከባድ ጎርፍ ምክንያት 179 የመሰረተ ልማቶችና 354 የንግድ ሱቆቿ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል፡፡ ጎርፉ የ 5ሺ 482 ከብቶች ሞትንም አስከትሏል፡፡

የሀገሪቱ የመከላከያ ና ደህንነት ምክር ቤትም በጎርፉ ምክንያት ለሶስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇልም ነው የተባለው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ጷግሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *