የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ የወንጀል ችሎት ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።

ፖሊስ የአሥራት ጋዜጠኞች በዋስትና ከእስር ቢፈቱ መረጃ ያጠፉብኛል ቢልም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን አልተቀበለውም።

ፖሊስ ከአራቱ የአሥራት ጋዜጠኞች መካከል በበላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ላይ ይግባኝ ጠይቆ የነበር ሲሆን በዋነኛነት ከኢመድኤ / INSA፣ ከሆስፒታል እና ከብሮድካስት ባለስልጣን መረጃ እንደሚያመጣ ጠቅሶ ከእስር ከወጡ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስለሆኑ መረጃ ያጠፉብኛል ብሏል ማለቱን አስራት ሚዲያ በፌስ ቡክ ገጹ ይፋ አደርጓል።

ይሁንና ፍርድ ቤቱ መረጃ ይመጣባቸዋል ከሚባሉት ተቋማት መረጃ ማጥፋት ሆነ ማዛባት እንደማይቻል ገልፆ የእስር ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ፖሊስ መረጃ እንዲታቀርብ ቀጠሮ ከሰጠ በኋላ ጋዜጠኞቹ በዋስትና እንዲለቀቁ ማድረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብሎታል።

የአሥራት ጋዜጠኞች በአራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲወጡ ከተወሰነላቸው በኋላ እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር የከፈሉ ሲሆን ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ በእስር እንዳቆያቸው ጠበቃቸው መግለፃቸው ይታወቃል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ጷግሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.