የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም በቀጣይ ሊከሰት ለሚችለው ወረርሽኝ መዘጋጀት ይኖርባታል ሲል አስጠነቀቀ ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ዓለም በቀጣይ ሊከሰት ለሚችለው ወረርሽኝ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሀገራትም ቢሆን በህብረተሰብ ጤና ላይ ሰፊ ምርምር እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2019 ታህሳስ ወር ላይ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በቻይና ሪፖርት ከተደረገ በኋላ አስካሁን በዓለማችን 27 ነጥብ 4 ሚለየን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 896 ሺ 842 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ የመጨረሻው ወረርሽኝ አይሆንም ያሉት ዶክተር ቴድሮስ ታዲያ ወረርሽኝ የሕይወት አንዱ ገፅታ እንደሆነ ታሪክ ያስተምረናል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ዓለም በቀጣይ ለሚከሰተው ወረርሽኝ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዝግጁ መሆን አለባት ማለታቸውን ሮይተረስ ዘግቧል፡፡

በትግስት ዘላለም
ጷግሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *