2 ነጥብ 7 ቢሊዮን በላይ ብር ዋጋ ያላቸው የጸረ ኤች አይቪ ኤድስ መድሃኒቶችን ለሕክምና ተቋማት ማሰራጨቱን የኢትዮጲያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የፀረ-ኤች አይ ቪ መድኃኒቶችን ለ1364 የጤና ተቋማት አሰራጨ ኤጀንሲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በ2012 በጀት ዓመት ለ1364 የጤና ተቋማት የፀረ-ኤች አይ ቪ እና ተጓዳኝ በሽታ መድኃኒቶችን አሰራጭቷል።

ኤጀሲው 2 ቢሊዮን 72 ሚሊዮን 794 ሺህ 122 ብር ወጪ ያላቸው የጸረ ኤች አይ ቪ እና ተጓዳኝ በሽታ መድኃኒቶችን መሰራጨቱን በኤጀንሲው የክምችትና የክትትል ባለሞያ የሆኑት አቶ በረከት ተዘራ ተናግረዋል፡፡

ስርጭቱም የጸረ ኤች አይ ቪ ህክምናውን ለሚሰጡ በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ 1 ሺህ 364 የጤና ተቋማት በኤጀንሲው ቅርጫፎች አማካኝነት 480 ሺህ 556 ሰዎች ማከም የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።

በየውልሰው ገዝሙ
ጷግሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.