የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን 1.5 ቢሊዮን ዶላር የብርድ ስምምነት ከቤላሩስ ጋር የተስማሙ ሲሆን የቤላሩስ ችግር ያለውጪ ሀይል ጣልቃ ገብነት መፈታት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
ፑቲን በቴሌቪዥን በሰጡት አስተያየት በመሪው Alexander Lukashenko የህገ መንግስት ማሻሻያ ለማድረግ የቀረበው ሀሳብ ምክንያታዊና ጊዜውን የጠበቀም ነው ብለዋል፡፡
የነሐሴ 9 ምርጫን ተከትሎ መላ ቤላሩስ አመፅ ላይ ነች፤ የመሪያቸው Lukashenko አገዛዝ እንዲያበቃም እየጠየቁም ነው፡፡
በመዲናዋ ሚንስክ ቢያንስ 100 ሺህ ሰዎች ጎዳናዎችን ሲያጥለቀልቁ የተያዙትን 500 ጨምሮ ፤ባጠቃለቃይ 774 ሰዎች በአመፁ ታስረዋል
የ 65 አመት ዕድሜው Lukashenko 9.5 ሚሊዮን ህዘብ ያለባትን ቤላሩስ እንደ አውሮፓውያኑ ከ 1994 ጀምሮ እየገዙ ነው
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በሔኖክ አስራት
መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም











