በሕንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አምስት ሚሊየን አለፈ፡፡

አሁን ህንድ  ከአሜሪካ ቀጥሉ ቫይረሱ ክፉኛ የጉዳት ሀገር ሆናለች፡፡

በሕንድ በአንድ ቀን ብቻ እስከ 90 ሺህ ሰዎች በኮቪድ-19 እየተያዙ ነው፡፡

ሮይተርስ እንዳለው እስካሁን ድረስ በአገሪቱ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፣ በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ ለታመሙ አልጋ እንዲሁም የኦክስጅን አቅርቦት እጥረት ተከስቷል።

በሕንድ የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ የመጣው በመጋቢት ወር ተጥሎ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ የምጣኔ ሃብቱን ለማነቃቃት በሚል ከተነሳ ወዲህ ነው።

ቫይረሱ ወደትንንሽ ከተሞች ከመሰራጨቱ በፊት እንደ ሙምባይና ደልሂ ያሉ ግዙፍ ከተሞችን ክፉኛ አጥቅቶ ነበር።

ሕንድ ምጣኔ ሃብቷን ክፍት ማድረግ በጀመረችበትና ሰዎች ወደ ስራ በተመለሱበት ወቅት የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ መምጣቱ ተስተውሏል።

ባለፉት ሳምንት ብቻ 600 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

እናም አሁን ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየን 020 ሺህ 359 የደረሰ ሲሆን፣ ባለፈው 24 ሰዓታት ብቻ 90 ሺህ123 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በዚህ ወር ብቻ ሆስፒታሎችና የእንክብካቤ ማዕከላት 2 ሺህ 700 ቶን ኦክስጅን የተጠቀሙ ሲሆን፣ በሚያዚያ ወር ግን 750 ቶን ብቻ ነበር ፍጆታቸው ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.