የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ከባህሬን ጋር ካደረጎት ታሪካዊ ስምምነቶች በኃላ “የአዲሱ የመካከለኛው ምስራቅ ጎህ” ተገለጠ ብለዋል ፡፡

ፕሬዝደንት ትራምፕ  ይህንን ያሉት  ሁለቱ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ መደበኛ የሚያደርጉ ስምምነቶችን ሲፈራረሙ ነው ፡፡

የሦስቱ አገራትን  ስምምነት  ትራምፕ ታሪካዊ ብለውታል ፡፡

የባህረ ሰላጤው አገራት እስራኤል ከተመሰረተችበት 1948 ጀምሮ እውቅና የሰጡ ሶስተኛ እና አራተኛ የአረብ ሀገራት ናቸው ፡፡

ትራምፕ ሌሎች ሀገሮችም ይህንኑ ይከተላሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጎ ተናግረዋል ፣ ፍልስጤማውያን ግን ጥያቄያቸው መፍትሄ እስካልተገኘ ድረስ የአረቡን ሀገራት ውሳኔ ኮንነዋል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል

መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.