በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ 94 ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት መሸኝቱን በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንሱል አስታወቀ፡፡

በሊባኖስ እስር ቤቶች ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ፣ በቤሩት ወደብ ፍንዳታ መጠለያ ያጡና ችግር ላይ የነበሩ፤ እንዲሁም በአሰሪዎች በደልና የመብት ጥሰቶች፣ የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸው እና መጠለያና ምግብ ያጡ የነበሩ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበርን እንዲሁም ሌሎች ድጋፍ የሚያደርጉ በጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በማስተባበር የአውሮፕላን ቲኬት ወጭዎችን እና ሌሎች የተለያዩ ድጋፎች እንዲደረጉላቸው ተደርጎ እንዲመለሱ ተደርጓል ሲል ነው ቆንሱሉ ያስታወቀው፡፡

94ቱ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበር በመጠለያ፣ በህክምና፣ በኮሮናቫይስ ምርመራዎች፣ አልባሳት፣ ምግብና መጠጦች፣ ማስኮች፣ ሳኒታይዘሮችን እንዲያገኙ በማድረግ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ነው ያስታወቀው፡፡

አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅትም (IOM) በተመሳሳይ የአውሮፕላን ቲኬት ወጭዎችን ሸፍኗል ሌሎችንም ድጋፎች አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ ቆንሱሉ ተጨማሪ 27 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንደሚሸኝም ነው ያስታወቀው፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *