የውጭ ዜና

በአሜሪካ በተከሰተው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ቤቱን ለቆ ለመሰደድ ተገዷል።

በአሜሪካ በተከሰተው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ኤሌክትሪክ ለማጣት ተገዷል።

ሳሊ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ ባስከተለው ሀይለኛ ዝናብና ማዕበል የአሜሪካን የባህረ ሰላጤ ዳርቻ ከጥቅም ውጪ ነው ያደረጋት፡፡

ዝናብ የቀላቀለው አውሎ ንፋሱ ፍሎሪዳ አላባማ ግዛቶችን መደብደቡን ቀጥሏል፡፡
ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል፡፡

ፍሎሪዳ ውስጥ የሚገኘው ፔንሳኮላ ክፉኛ የተጎዳ ሲሆን ጎርፍ የወሰደው የጭነት መርከብ ባህሩን የሚያጋምሰውን ድልድይ የተወሰነው ክፍል እንዲደረመስ አድርጎታል፡፡

ፔንሳኮላ ከተማ ላይ አውሎ ንፈሱ የአራት ወራት ዝናብ በአራት ሰአታት ውስጥ እንዲመጣ ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አውሎ ንፈሱ ከነህር ዳርቻው ወደ ሰሜን የሚሄድ ሲሆን 550 ሺህ ነዋሪዎች በጨለማ መኖርያቸውን ለቀው እንዲሄዱ አስገድዷል።

ሳሊ አትላንቲክ ውቅያስ ላይ ከሚከሰቱ በርካታ አውሎ ንፋሶች መካከል አንዱ ነው፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *