የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አል ሳራጅ ስልጣናቸው ሊያስረክቡ ነው፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድረጅት እውቅና የተሰጠው የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አል ሲራጅ ስልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ ነው ያስታወቁት፡፡

ፋይዝ አልሲራጅ ከሀገራቸው የቴሌቪዥን ጣበያ ጋር ባደረጉት ንግግር ነው ለህዝባቸው ያስተላለፉት፡፡

በመሆኑም በሚቀጥለው ጥቅምት ወር ላይ ስልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ አስታውቀዋል፡፡

ብሉምበርግ የዜና ወኪል እንዳስነበበው በሀገሪቱ እየተፈጠረ ባለው ነገር ደስተኛ እንዳልሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ለተተኪያቸው ማስረከብ እንደሚፈልጉ ነው የተናገረው፡፡

በሊቢያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና የተሰጠው የፋይዝ አል ሳራጅ መንግስት እና በካሊፋ ሀፍታር የሚመራው መንግስት በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ከገቡ ቆይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግጭቱን ለማርገብ ሁነኛ ያሉት አማራጭ ስልጣናቸውን መልቀቅ እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

ፋይዝ አል ሳራጅ ከአምስት አመታት የስልጣን ቆይታ በኃላ ነው ስልጣናቸውን ለመልቀቅ የወሰኑት፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *