ሶማሊያ አዲሰ ጠቅላይ ሚኒስትር አግኝታለች

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ  – ሞሃመድ ሁሴን ሮቤልን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ ፡፡

ፕሬዚዳንቱ  አዲሱን ጠቅላይ  ሮቤል የመረጥኩት  “በመንግሥት ግንባታ ጥረቶች እና በብሔራዊ  ልማት ዕቅዶች  ወደፊት ለመራመድ ባላቸው  ዕውቀት ፣ ልምድ  እና ችሎታ”  ነው ብለዋል ፡፡

አዲሲ ተመራጭ  ሮብል የፓርላማውን እምነት ካገኙ ሐምሌ 25 ቀን በፓርላማው ያለመተማመን ድምፅ የተባረሩትን ሀሰን አሊ ኻይርን ይተካሉ ፡፡

ፕሬዝዳንት ፋርማጆ በመግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ  “ሀገሪቱን ወደ ምርጫ የሚያደርስ ብቃት ያለው መንግስት በአስቸኳይ እንዲቋቋም  እና የፀጥታ  ተቋማትን  እንዲያጠናክሩ  ፣ መሰረተ ልማት ዝርግታዎችንም እንዲፋጥኑ   ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉ” አሳስበዋል ሲሉ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል ፡፡

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር  ሮብል  ለሶማሊ ፖለቲካ  አዲስ ሰው ናቸው ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *