በኮቪድ -19 ምክንያት በዓለም ዙሪያ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሕፃናት ቁጥርን 15 በመቶ እንዲጨምር እንዳደረገው የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው ይህ የድህነት መጨመር ተጨማሪ 150 ሚሊዮን ሕፃናትን የሚወክል በቂ የትምህርት ፣ የመኖሪያ ቤት ፣ የተመጣጠነ ምግብ ፣ የጤና አገልግሎት ፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና አጠባበቅ አለመኖሩን ያሳያል ፡፡
ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በድህነት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር አሁን ወደ 1.2 ቢሊዮን የሚጠጋ እንዲሆን እንዳደረገው ሲኤን ኤን ፖርቱን ጠቅሱ ዘግቧል ፡፡
ሪፖርቱ ወደ 80 የሚጠጉ አገራት መረጃን መሠረት ያደረገ ነው ፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 8 ቀን 2012 ዓ.ም











