የሀገር ውስጥ ዜና

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ሲሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት አመለከቱ።

ምክር ቤቱምበቀረበው ሪፖርት ላይ እየተወያየ ነው፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት አጭር ሪፖርት ኮቪድ-19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሃገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት ከተከሰተ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ዶ/ር ሊያ ባቀረቡት ሪፖርት አመልክተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ

መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *