በግብፅ ስዊዝ ፣ ካፈር ኤል ዳዋር ፣ በናይል ዴልታ ፣ ካይሮ ፣ አሌክሳንድሪያ እና አስዋን ከተማ ውስጥ አልሲሲ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ ሰልፍ ተነስቷል፡፡
የግብፅ ፀጥታ ኃይሎች በሰልፈኞች ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎም አስዋን ውስጥ የሚገኘው የፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤት በሰልፈኞች ተቃጥሏል ነው የተባለው ፡፡
ፀረ-አል ሲሲ ተቃዋሚዎቹም በፖሊስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ና የፖሊስ ሀይሉም ሲያፈገፍግ የሚያሳዩ ምስሎችም በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ እየተዘዋወረ አንደሚገኝም ዘገባው ጠቅሷል፡፡
በዋና ከተማዋ ካይሮም ካፌዎችን ለአድማ በከፊል ዝግ መሆናቸውንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡
የተቃውሞ ሰልፉም መሀመድ አሊ የተባለ አክቲቪስት በሀገሪቱ ያለውን ፍትህ መጓደል ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እንዲያቃወምና ሀገሩን እንዲታደግ በጠራው ሰልፍ መሰረት የተካሄደ መሆኑንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡
ባለፈው ዓመት መሀመድ አሊ የግብፅ መንግስት በሙስና ውስጥ ተዘፍቆ ሀገሪቱን ለከፋ እግር እንደዳረጋት የሚያሳይ መረጃን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡
ይህንንም ተከትሎ ግብፃውያን ከፍተነኛ ተቃውሞ አስነስተው የነበረ ሲሆን የሀገሪቱ መንግስት ተቃውሞውን ለማብረድ ቢያንስ 4 ሺ ሰዎችን ማሰራቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በትግስት ዘላለም
መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም











