ሱዳን አሸባሪዎችን ስፖንሰር ታደርጋለች በሚል የአሸባሪ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ካስገባቻት አሜሪካ ጋር ከዝርዝሩ እንድትሰርዛት የተጀመረው ድርድር ፍሬ ሊያፈራ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡
ሱዳን ከፍተኛ ልኡኳን ከአሜሪካ ባለስልጣኖች ጋር እዲወያዩ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬት ልካለች፡፡
ይሄ ውይይት ከአሸባሪ ዝርዝሩ እንድትሰረዝ እደሚያደርጋት ይጠበቃል፡፡
ከፍተኛ ልኡኩ የሚመራው በሀገሪቱ መሪ ጀነራል አብድል ፈታህ አል ቡርሀን ነው፡፡
አሜሪካ ሱዳንን በሀገሯ ለ 5 አመታት መጠለያ የሰጠችውን ኦሳማ ቢላደንን ጨምሮ አክራሪ ኢስላማዊ ቡድኖችን ትደግፋለች ብላ አሸባሪ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ የከተተቻት እንደ አውሮፓውያ በ 1993 ነበር፡፡
የድርድሩ አካል እንዲሆን የተደረገው ፤ አሜሪካ በሽብር ጥቃት ተጎጂ ለሆኑ ቤተሰቦች ሱዳን 300 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ትፈልጋለች፡፡
የአሜሪካ መንግስት ሱዳን ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታስተካክል እየሞከረች መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
በሔኖክ አስራት
መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም











