የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወር መጨረሻ ወደ ኬፕታወን እና ጆሃንስበርግ አቋርጦት የነበረውን በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።

አየር መንገዱ የኮሮና ቫይረስ በመስፋፋቱ ምክንያት የደቡብ አፍሪካ ከተማ ወደ ሆኑት ጆሃንስበርግ እና ኬፕ ታውን በረራዉን ዳግም እንደሚጀምር ገልጿል፡፡

አየር መንገዱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብዙዎቹን ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች በማቋረጥ ትኩረቱን ወደ እቃ ጭነት ወይም ካርጎ አዙሮ ነበር።

አሁን ላይ በርካታ አገራት በቫይረሱ ምክንያት ጥለውት የነበረውን እገዳ በማላላት ላይ በመሆናቸው ጎብኚዎች ወደ አገራቸው እንዲገቡ በማድረግ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከዚህ በፊት ወደ ዱባይ፣ዊንድሆክ እና ሌሎች ከተሞች አቋርጦት የነበረውን በረራ ዳግም ጀምሮ ደንበኞቹን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።

ከመስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮም ወደ ጆሃንስበርግ እና ኬፕታወን ከተሞች ዳግም በረራውን እንደሚጀምር አስታውቋል።

በቀጣይም ሌሎች ተጨማሪ የዳግም በረራዎቹን እንደሚያካሂድም አየር መንገዱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

የአፍሪካ ግዙፉ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2012 በጀት ዓመት 3 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን መግለጹ አይዘነጋም፡፡

በዚህም አየር መንገዱ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች አቅማቸዉ በእጅጉ መዳከሙ ሲገለጽ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለማቀፍ ደረጃ ካሉ አየር መንገዶች ሁሉ ህልዉናቸዉን አስጠብቀዉ ትርፍ ማገኘት ከቻሉ 3 አየር መንገዶች ዉስጥ አንዱ ለመሆን ችሏል፡፡

በደረሰ አማረ
መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *