በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሁለት መቶ ሺህ አለፈ።

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ዘገባ በሃገሪቱ በአሁን ሰዓት6.8 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

ይሁን እንጂ በሃገሪቱ የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየጨመረ በመጣበት ባለፈው ኅዳር ወር ላይ ፕሬዝደንት ትራምፕ በአሜሪካ በቫይረሱ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ እስከ 200ሺህ መካከል ከሆነ በሽታውን የመከላከላችን ሥራ ውጤታማ ሆኗል ማለት ነው ብለው ነበር።

ይሁንና የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የተከሰተውን ወረርሽኝ አያያዝ በተመለከተ በተደጋጋሚ ተችቷል ፡፡

የዴሞክራቲክ ፕሬዝዳንት እጩ ጆ ባይደን “ዶናልድ ትራምፕ ባለፉት ስድስት ወራት በውሸታቸው እና ሃገርን መምራት የሚያስችል ብቃት ስላልነበራቸው በታሪክ ውስጥ በአሜሪካ ከታዩት ከፍተኛ ጥፋቶች መካከል አንዱን ተመልክተናል” ብለዋል ፡፡

ነገር ግን ይህን የማይቀበሉት ትራምፕ እና አስተዳደራቸው አስገራሚ ሥራ እንደሠሩ በመግለጽ የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ለሰሯቸው ስራዎች “A +” ሰጥተዋል ፡፡

እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ በሃገሪቱ ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋ ፋባቸው ግዛቶች በክረምት ወራት ላይ ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይሄዳል የሚል ስጋት አለ፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.