ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ መገደሉን ተከትሎ ሁከት በማስነሳት እና በሌሎች ጉዳዮች ተጠርጥረው በአስር ላይ የነበሩት አቶ ልደቱ ዛሬ በትናንትናው ዕለት ምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል።
የአቶ ልደቱ ጠበቃ አቶ አብዱል ጀባር ሁሴን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ብሩ የተከፈለ ቢሆንም ዛሬ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ብናመራም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አልተከበረም ብለዋል።
የምርምራ ቡድኑ አቶ ልደቱ እንዲፈቱ ባስተላለፈው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ላይ ምንም ማለት አንችልም መባላቸውን ጠበቃው ነግረውናል።
በመሆኑም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን እንዲያስከብር ለፍርድ ቤት አቤቱታ እናስገባለን ሲሉም ተናግረዋል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም











