የደቡብ ኮሪያ የመከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከሆነ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች አንድ የደቡብ ኮሪያን ባለስልጣንን ተኩሰው ከገደሉ በኋላ አስከሬኑን አቃጥለዋል፡፡
ይህንን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር አውግዟል ብሏል ሲኤን ኤን ፡፡
ሴኡል ግለሰቡ በድንበር አቅራቢያ ከነበረ የድንበር ተቆጣጣሪ ጀልባ ላይ መጥፋቱን እና በኋላ ላይ አካሉ በሰሜን ኮሪያ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ባህር ላይ መገኘቱን ተናግራለች፡፡
የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተኩሰው ከገደሉት በኋላ አስከሬኑ ላይ ነዳጅ አርከፍክፈው እሳት እንደለኮሱበት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡
ሚኒስቴሩ በተለያዩ የስለላ ምንጮች በመታገዝ እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሱንም አያይዞ ገልጿል፡፡
ይህንና ሰሜን ኮሪያ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስተጠት ተቆጥባለች፡፡
በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም











