የአፍሪቃ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲ.ዲ.ሲ.) ኃላፊ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የአፍሪቃ ሀገራት ያደረጎትን ርብርብ አድንቀዋል፡፡
አፍሪቃ ከየካቲት ወር ጀምሮ ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ተጠቂዎች ሲገኙ
34,000 ሰዎችን ሞት አስተናግዳለች፡፡
እነዚህ ቁጥሮች በአውሮፓ ፣ በእስያ ወይም በአሜሪካ ካሉ እጅግ በጣም አናሳ ናቸው ፡፡አሁን አሁን የተጠቂዎች ቁጥር መቀነሳቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቱችም እየወጡ መሆናቸውን አስረድተዋለ፡፡
በአፍሪቃ ሲዲሲ ኃላፊ ጆን ንከንጋንግ ለቢቢሲ ኒውስዴይ ፕሮግራም እንደተናገሩት የቅድመ መከላከልና ጥብቅ የሆኑት ገደቡችን መጣል የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል ፡፡
የአፍሪቃ ሲዲሲ 55 አባላት ያሉት የአፍሪካ ህብረት የጤና ድርጅት ነው ፡፡
ከአንድ ቢሊዮን በላይ ህዝብ ያለው አህጉር በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥሩ ከ 5% በታች ሲሆን የሞት መጠኑም 3.6% መሆኑን ሲዲሲ በድረገጹ አስፍሯል፡፡
በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም











