አቶ ልደቱ አያሌው በዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ዛሬ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የፍርድ ቤት ውሳኔ አለመከበር ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አደጋ ነው ብሏል።

አላስፈላጊ እስር ማስቀረትና የዋስትና መብት ማክበር እንደሚያስፈልግም ኮሚሽኑ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እንዳሉት
“የሰብዓዊ መብቶች መከበር ዋና ዋስትናው የፍርድ ቤት ውሳኔ መከበር በመሆኑ፤ አቶ ልደቱ አያሌውን ጨምሮ በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸውና የዋሰትና ሁኔታውን አሟልተው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጠላቸው ታሳሪዎች በሙሉ በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊፈቱ ይገባል” ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.