ዶናልድ ትራምፕ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ለማድረግ አለመዘጋጀታቸው ተነግሯል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሩ ምርጫ የሚሸነፉ ከሆነ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ለማስተላለፍ እንደሚቸገሩ ፍንጭ ሰጥተዋል ተብሏል፡፡

በነጩ ቤተመንግስት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጥያቄው ሲነሳባቸው ‹‹ መልካም ፡፡ የሚሆነውን ነገር ማየት ይኖርብናል፡፡ ›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ትራምፕ አያይዘውም የምርጫው ውጤት ምናልባትም እስከ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሊሄድ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በፖስታ ቤት በኩል የሚደረግን ምርጫ ፕሬዝዳንቱ ክፉኛ በማውገዝ ላይ ናቸው እንደ ሲኤን ኤን ዘገባ፡፡

በፖስታ ቤት የሚደረግ ምርጫን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ይቀንሳል ተብሎ ታምኗል፡፡

በአሜሪካ ምርጫ ሊካሄድ የሚቀሩት 40 ቀናት ናቸው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ግን ከተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን ያነሰ ድጋፍ እንዳላቸው የህዝብ አስተያየት መለኪያዎች ያሳያሉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.