በደቡብ አፍሪካ የመንግስትን ንብረት ለፖርቲ አገልግሉት እንውል አድርገዋል የተባሉ የመከላከያ ባለስልጣ የሶስት ወር ደመወዛቸውን ተቀጡ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሯ ቅጣታቸውን የተከናነቡት በዚህ በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ የሀገሪቱ ገዢ ፓርቲ አመራች በአየር ሀይሉ አውሮፕላን ወደ ዚምባብዌ እንዲበሩ በመፍቀዳቸው መሆኑን ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገቧል፡፡

በዚህ ጉዞም እርሳቸውም አብረው እንደነበሩ ተጨምሮ ተዘግቧል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ሚንስትሯ የሶስት ወር ደሞዛቸው እንዲቋረጥ በማድረግ ገቢው ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ለሚደረገው እንቅስቃሴ ገቢ እንዲደረግ ወስነዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ቢሮ ግን እርሳቸው ለስራ ጉዳይ ወደ ዚምባብዌ እንደሄዱ እግረ መንገዳቸውን ግን ሰዎችቹን አብረዋቸው እንዲሄዱ እንደፈቀዱላቸው አስረድቷል፡፡
ጉዞ ፈጽሙ ለፖለቲካ ስራ አልነበረም ነው ያለው፡፡

ሚኒስትር መስራ ቤቱ እንዲህ ቢልም ፕሬዝደንት ራማፎሳ ግን የሚንስትሯ ተግባር ስህተት ነው ብለውታል።

ፕሬዝደንቱ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ገዢውን ፓርቲ እና ባለስልጣናትን ከተዘፈቁበት ሙስና እና ብልሹ አሠራር እንደሚያላቅቁ ቃል ገብተው ነበር።

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም የሚኒስትሯን ተግባር አሳፋሪ መሆኑን በመግለጽ ፤እርምጃው በቂ አይደለም ሲሉም ድምጽ አሰምተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.