የቀድሞ የማሊ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

የማሊ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እዳሳወቀው የሀገሪቱ ወታደራዊ የሽግግር ፕሬዝዳንት ባህ ንዳው ወታደር ያልሆነ ሲቪል ጠቅላይ መኒስትር ሾመዋል፡፡

ንዳው የቀድሞውን ዲፕሎማት ሞክታር ኦዋኔን የጠቅላይነቱን ቦታ ሰጥተዋቸዋል፡፡

ኦዋኔ እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2004 እስከ 2011 የማሊ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡

እንደ አውረፓውያኑ ከ 1995 እስከ 2002 ድረስ ደግሞ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማሊ ቋሚ ተወካይ ነበሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ህብረት ኢኮዋስ የዲፕሎማሲ አማካሪ ሆነው ነበር፡፡

የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ባህ ንዳው’ን የሽግግር ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ መርጠዋቸው ባለፈው አርብ ተሾመዋል፡፡

ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ በማሊ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እዲነሳ ወታደር ያለሆነ ሰው ፕሬዚዳንት እዲሆን ኢኮዋስ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጦ ነበር ፡፡

በመቀጠልም የኢኮዋስ ሀላፊዎች ማዕቀቡ ሊነሳ የሚችለው ወታደር ያልሆነ ሲቪል ጠቅላይ ሚኒስትርም ሲሾም ነው ብለው አርብ ዕለት ገልፁ፡፡

ባለፈው ወር በማሊ ከተፈፀመው መፈንቅለ መንግስት በኋላ ፤ በዚህኛው ሹመት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲቪል እዲሆኑ መደረጉ በኢኮዋስ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ዕድል ሊከፍት ይችላል ተብሏል፡፡

የመፈንቅለ መንገስቱ መሪ ኮሎኔል ጎይታ ምክትል ፕሬዝዳንት በሆኑበት ሁኔታ የስልጣን ሚዛኑ ወታደሩ ጋር ሆኖ እንደማይቀጥል ግን ማረጋገጫ የለም እየተባለ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
መስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.