እውን የፋና ላምሮት 8222 የአጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀበያ ስራ አቁሞ ነበር?

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በ11 ዙሮች ሲያካሂደው የነበረውን የፋና ላምሮት የሙዚቀኞች ውድድር ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ መስከረም 17 ቀን 2013 ዓ.ም ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ግማሽ ሚሊዮን ብር በሚያሸልመው በዚህ ውድድር የመጨረሻው ዕለት በተደረገ ውድድር መቅደስ ግርማ በአንደኝነት ኤልያስ ተክለሀይማኖት ሁለተኛ እንዲሁም ዮናታን ክብረት በሶስተኛነት ማጠናቀቃቸውም አይዘነጋም።

ይሁንና በውድድሩ ፍጻሜ ላይ ተመልካቾች በአጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚሰጡበት 8222 መበላሸቱ በመድረኩ ላይ ተገልጾ ነበር።

በዚህ ምክንያትም በርካቶች ቅሬታ እንዳላቸው እና የተመልክቾች ድምጽ ሆን ተብሎ ተጭበርብሯል በሚል በተለያዩ መድረኮች ላይ አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ናቸው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም እውን በዕለቱ የፋና ብሮድካስቲንግ የአጭር የጽሁፍ አስተያየት መቀበያ የሆነው 8222 ተበላሽቶ ነበር? ሲል ኢትዮ ቴሌኮምን ጠይቋል።

በኢትዮ ቴሌኮም ዋና የሽያጭ ኦፊሰር የሆኑት አቶ መሀመድ ሀጂ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ፋና ላምሮት ከተመልካቾቹ የጽሁፍ መልዕክት ይቀበልበት የነበረው 8222 ኮድ በዕለቱ በአንዴ ከአንድ ሺህ በላይ መልዕክቶችን እያስተናገደ ነበር።

ይሁንና ይህ አጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀበያ ኮድ በአንዴ የመቀበል አቅሙ 200 መልዕክቶችን ብቻ ነበር ብለዋል።

በመሆኑም ከአቅም በላይ መልዕክቶች ከተመልካቾች በመምጣታቸው የአጭር የጽሁፍ መቀበያ ኮዱ በአቅም ማነስ ምክንያት ተበላሽቶ ከአገልግሎት ዉጪ እንደነበር አቶ መሀመድ ነግረውናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.