ለአገር ክብር ዋጋ የሚከፍል ዘመናዊ የፖሊስ ሰራዊት መገንባቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ።

የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን ከራስ በላይ ለህዝብና ለሃገር በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ የተለያዩ ትርኢቶችን አቅርቧል፡፡

በትርኢቱም የተለያዩ የፀረ ሽብር ተግባራት ሲከሰቱ ፈጣን ምላሽ በመስጠትና ውስብስብና የተቀነባሩ ወንጀሎችን ለማክሸፍ የሚረዱ እንደሂሁም የፌደራል ሰራዊት አባላቱ አሁን ያሉበትን ደረጃ የሚያሳዩ የተለያዩ ወታደራዊ ትእይቶችን አሳይተዋል፡፡

በተለይም የኮማንዶ አባላቱ ለሃገር ደህንነትና ሰላም ከፊት በመሰለፍ የትኛውንም ህገ ወጥ ጥቃትን ለመመከት የሚያስችል አቅም እንዳለው ያሳየበት ትርኢት መሆኑም በመድረኩ ተነግሯል፡፡

በዚህ ትርኢት ላይ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የተገኙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ለሰራዊቱ መልእክትን አስተላልፈዋል፡፡

በሃገሪቱ የለውጥ ሂደት ላለፍት 2 ዓመታት ሲሰራ የቆየውን ሪፎርም ዛሬ ፍሬ ማፍራቱንና ሃገር ወዳድ ለሃገሩ ቅድሚያና የሚሰጥና ለሃገር ክብር የማይራደር ሰራዊት ለመገንባት መቻሉን በማድነቅ ይሄንን ልዩ ትርኢት ላቀረቡት የሰራዊት አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ሰራዊቱ ፤ዝናብ፤ፀሃይና ሌሎችም እንቅፋቶች የማይበግረው ፤ዛሬን አጥሮቶ ነገን አሻግሮ የሚመለከት ጠንካራና እጅ የማይሰጥ እንዲሆንም ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ለሰራዊቱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ሰራዊቱንም እድገት የበለጠ ለማዘመንንም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በቀጣይ ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረጉ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ።

በመጨረሻም ፖሊስ የኢትዮጲያ ሰላምና የኢትዮጲያ ኩራትም ይሆን ሲሉ ለሰራዊቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ
መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *