በቶጎ የመጀመርያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ተመረጠች፡፡

የቶጎው ፕሬዝዳንት በሀገራቸው ታሪክ የመጀመርያዋን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመትን ሰጡ፡፡

የ60 አመቷ ቪክቶሪ ቶሜጋ ዶግቤ የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በፕሬዝዳንቱ አማካኝነት ሹመት አግኝተዋል፡፡

ዶግቤ የቀድሞ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ኮሚ ሴሎምን ተክተው ነው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት፡፡

ኮሚ ሴሎም ባለፈው አርብ እለት በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣናቸው መነሳታቸው ይታወሳል፡፡

ኮሚ ሴሎም ከ2015 አንስቶ እስካሁን የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተመረጡት ዶግቤ በቶጎ ህዝብ እጅግ የሚወደዱ እንደሆነ ነው አልጀዚራ ያተተው፡፡

ከዚህ በፊት የፕሬዝዳንቱ አማካሪ እንዲሁም የጽህፈት ቤታቸው ዳይሬክተር ሆነውም አገልግለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የወጣቶች ሚኒስትር ሆነውም እንደሰሩ ነው የሒወት ታሪካቸው የሚያሳየው፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራምም ከሰራችባቸው ተቋማቶች መካከል ይገኙበታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *