ትራምፕና ባይደን የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ክርክር አካሄዱ፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና እጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ክርክራቸው ማካሄድ ጀምረዋል፡፡

በርካቶች በተከታተሉት በዚሁ ክርክር በትራምፕና ባይደን በርካታ የሓሳብ ፍጭቶች ተነስተዋል፡፡

በተለይም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ክፍኛ እየተጎዳች ላለችው አሜሪካ ተገቢውን ምላሽና ሃላፊነት አልሰጡም ተብለው በተቃዋሚያቸው ጆን ባይደን ለትራምፕ ለተነሳውን ሃሳብ፤
ትራምፕ የባይደንን ሃሳብ ውድቅ ከማድረግ አልፈው ባይደንን ምንም እንኳን በጣም ታሳዝናክ ምንም አታውቅምና የተማርክበት እጅግ ዝቅተኛ ነበር ሲሉ አስገራሚ ምላሾችን ሰተዋል፡፡

እንዲሁም ባይደን በዚሁ ጊዜ ሃገሪቱን መርተዋት ቢኖር ኖሮ ህዝብ በሙሉ ያልቅ ነበር ሲሉ ምላሽ ሰተዋል፡፡

በአጠቃላይ የ 90 ደቂቃ ፍክክሩ እጅግ ንዴትና ስድብ የተሞላት ነበር ማለት የሚያስደፍር እንደሆነ ተነግሯል በሁለቱም ወገን ፡፡

ፍክክሩ አሁንም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ትራምፕና የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ባይደን ከሚያካሂዱት የገፅ ለገፅ ክርክር በተጨማሪ ሌሎች የፍክክር ሃሳቦች ይጠብቃቸዋል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

በየውልሰው ገዝሙ
መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *