አዘርባጃን እና አርሜኒያ ወደ ግጭት ከገቡበት ቀን አንስቶ እስካሁን 2 ሺህ 300 የአርሜኒያ ወታደሮች መሞታቸው ተነገረ፡፡

የአርሜኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደተናገሩት ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት አንስቶእስካሁን ድረስ 2ሺህ 300 ያህል ወታደሮች ሂወታቸው እንዳለፈ ነው የተናገሩት፡፡

አናዱሉ የዜና ወኪልም ሁለቱ ሀገራት ወደ ለየለት ጦርነት መግባታቸውን ጠቅሶ በርካታ ንጹሀን ዜጎች የግጭቱ ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ ሲል አስታውቋል፡፡

ከአራት ቀናት በፊት ነበር ሁለቱ ሀገራት በታሪክ እየተወዛገቡበት ባለው የናጎሮኖ ተራራ የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ግጭት ውስጥ የገቡት፡፡

በዚህችው ተራራ ምክንያትም አዘርባጃን እና አርሜኒያ በ1988 ለስድስት አመታት የዘለቀ ጦርነት አድርገው 30ሺህ ያህል ዜጎችን ገብረዋል፡፡

አንድ ሚሊየን ዜጎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና መላው የአለም ማህበረሰብ ናጎሮኖ ተራራ የአዘር ባጃን እንደሆነ ነው የሚያወቀው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *