የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለሰባት የጤና ተቋማት ወደ ውጭ አገራት ለሚጓዙ መንገደኞች የኮሮና ቫይረስ ምርምራ እንዲያደርጉ ፈቀደ።
የግል የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማዕከላት እንደ ልብ አለመገኘት በርከት ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቅሬታ ሲያስነሳ ቆይቷል፡፡ በተለይም የዉጭ ጉዞ ያለባቸዉ ሰዎች አብዝተዉ ሲያማርሩ ቆይተዋል፡፡ የምርመራ ዉጤት ማፍጠኛ ገንዘብ መጠየቃቸውንም መንገደኞቹ ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡ አሁን ላይ ታዲያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቀደም ሲል ምርመራ ሲያደርግ የነበረዉን ኢንተር ናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስን ጨምሮ 7 የግል ሆስፒታሎች የኮቪድ 19 ምርመራ እንዲያደርጉ ፈቅጃለሁ […]