የማላዊ ፓርላማ ከአንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት የተለገሰ 200 ሺህ ኮንዶሞችን አልቀበልም አለ፡፡

ኤድስ ሄልዝኬር ፋውንዴሽን [AHF] ከ 500 በላይ የሚሆኑ ለትርፍ ያልተቋቋሙ አለም አቀፍ ድርጅቶች የመሰረቱት ፋውንዴሽን ነው፡፡

ይህ ተቋም ለማላዊ ያቀረበውን ከ 200 ሺህ በላይ ኮንዶሞች የሀገሪቱ ፓርላማ ስጦታውን እንደማይቀበለው ውድቅ አድርጓል፡፡

ከኤድስ ጤና ፋውንዴሽን [AHF] ለስጦታ የቀረቡ ከ 200 ሺህ በላይ ኮንዶሞች በማላዊ የሚገኙ ህግ አውጭዎች ውድቅ አድርገውታል፡፡

አሁን ላ ኮንዶሞቹ በሀገሪቱ ፓርላማ ሕንፃዎች በሚገኙ መፀዳጃ ቤቶች ውስጥ እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማ አባል የሆኑት ሪቻርድ ቺምዌንዶ በበኩላቸው የፓርላማ አባላት ኮንዶም መግዛት ስለሚችሉ እንደዚህ አይነት ድጋፍ አያስፈልጋቸውም ብለዋል፡፡

ቺምዌንዶ እንደገለጹት በጋዜጣ ስለ ልገሳው ያወጣው ዘገባ የፓርላማ አባላቱን ዝና እና ክብር ጎድቷል ብለዋል፡፡

ማላዊ ኔሽን ጋዜጣ በሪፖርቱ የፓርላማ ምንንጮችን ጠቅሶ ምክር ቤቱ በየ ወሩ ወደ 10 ሺህ ለሚጠጉ ኮንዶሞች ወጪ እንደሚያወጣ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜም የአቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው ገልጧል፡፡

ምክትል አፈ-ጉባኤ ማዳልዮሶ ካዞምቦ ይህ ትክክል አለመሆኑን በመግለጽ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

በደረሰ አማረ
መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *