የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ኮቪድ ነፃ የሆነ ቱሪዝምን ለመተግበር ከሆቴል ባለሀብቶች ጋር እየመከረ ነው።

ሚንስቴሩ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለወራት ተቀዛቅዞ የቆየውን የቱሪዝም ዘርፉን እንቅስቃሴ በተወዳዳሪነት እንደገና ለማስጀመር እና ከኮቪድ ነፃ የሆነ ቱሪዝም ለመተግበር የኮቪድ ሰርተፊኬሽን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የጉብኝት ፕሮቶኮል ላይ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ከሆቴል ባለሀብቶች ጋር በመመካከር ላይ ይገኛል።

ፕሮቶኮሉ የዓለም ቱሪዝም ድርጅት፣የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጡትን መመሪያ እንዲሁም የጤና ሚንስቴር ምክረ ላይ በመመርኮዝ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

የፕሮቶኮሉ ዓላማ የጎብኝዎችን፣ የዱር እንስሳትን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ሰራተኞችን ፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጤና እና ደህንነትን ማረጋገጥ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያን የድህረ ኮቪድ የጉብኝት መዳረሻ ማድረግ፣ የቱሪዝም ኢኮኖሚውን ማነቃቃት፣ የንፅህና ባህላችንን በማሳደግ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ተወዳዳሪ ማድረግም ነው ተብሏል።

ፕሮቶኮሉ ቱር ኦፕሬተሮች፣ የጉብኝት መዳረሻ ቦታዎች፣ ሆቴሎችና ሁነቶች ላይ ተግባራዊ ይሆናልም ተብሏል።

የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳሁን እንዳሉት ፕሮቶኮሉ ለዓለም አቀፍ ቱሪዝም ድርጅት ተልኮ ጥሩ ምላሽ ማግኘቱን ተናግረዋል።

በመሆኑም የአገልግሎት ሰጪ ተቋሞቻችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ሆነው መገኘትና ጎብኝዎች ችግር ሳይገጥማቸው ተስተናግደው እንዲሄዱ ማድረግ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.