የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ መረጃ በመስጠት አድናቆት ተቸራቸው።

የመረጃ ነፃነት ቀን ህይወትን ለመታደግ፣መተማመንን ለማስፈንና ለብሩህ ተስፋ፤ በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ 5ኛ ጊዜ በሀራችን ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።

የመረጃ ነፃነት ህግን የማስተግበርና አፈፃፀሙን የመከታተል ሀላፊነት በህግ የተሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም ፤ ቀኑን አስመልክ በአዳማ ከተማ ባሰናዳው መድረክ ፤ የኮሮና ወርሽኝ በአለማችንም በሀገራችንም ዘርፈ ብዙ ቀውስ በፈጠረበት በዚህ ወቅት ፤ መረጃ ህይወትን ያድናል ተብሏል።

የህዝብ ዕምባ ተቋም ዋና ዕምባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ሀይሌ ፤ኮሮና ወረርሽኝን አስመልክቶ ህዝቡ ህይወቱን ሊያድን የሚችልበትን መረጃ ሳይሰለቹ በቀን በቀን ለሚሰጡት ለጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰና ለባልደረቦቻቸው ምስጋናና አድናቆት ይገባል ብለዋል።

ታዳሚውም ለዚህ ምሳሌ ለሆነ ተግባራቸው ምስጋናውን በጭብጨባ እንዲገልፅ በጠየቁት መሰረት፣ ታዳሚው ምስጋናና አድናቆቱን በሞቀና በደመቀ ሁኔታ በጭብጨባ ገለጿል።

መገናኛ ብዙሐንና ጋዜጠኞችም ወረርሹኙን አስመልክቶ ለህብረተሰቡ እያቀረቡ ያሉት መረጃ ህይወት አድን ነውና ምስጋናና አድናቆት ይገባቸዋል ተብሏል።

በአሁን ሰአት የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ከቀኑ መሪ ቃል ተወስዶ ስያሜ ያገኘ ወረቀት እያቀረቡ ይገኛሉ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *