ዳሸን ባንክ ለገበታ ለአገር ፕሮጀክቶች 30 ሚሊዮን ብር ሰጠ።

ከአንድ ወር በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይፋ ላደረጉት ጎርጎራ፣ወንጪ እና ኮይሻን እንደ አዲስ ለማልማት 6 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ መግለጻቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ዳሸን ባንክ ለነዘህ ፕሮጀክቶች ለእያንዳንዳቸው 10 ሚሊዮን በድምሩ 30 ሚሊዮን ብር መስጠቱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

ባንኩ ከዚህ በተጨማሪም ለማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት 170 ሚሊዮን ብር መመደቡንም ገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *