ሰዓሊ ዮሃንስ ታደሰ አረፉ።

ሰዓሊ ዮሃንስ ታደሰ ከአባታቸው ከአቶ ታደሰ ወልደሩፋኤል እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘነበች ገድሌ ጥር 5 ቀን 1943 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ነበር የተወለዱት።

እድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስም በዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት የ1ኛ እና 2ተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

ሰዓሊ ዮሃንስ በነበራቸው የስዕል ዝንባሌ
በኪነጥበብ (Art school) ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ሙያዊ የኪነጥበብ እና ስዕል ትምህርታቸውን ተከታትለው በማጠናቀቅም ተመርቀዋል።

ሰዓሊ አቶ ዮሃንስ በሙያቸው የቤተሰብ መምሪያ ሎጎን ፣ በብሄራዊ ሎተሪ፣ሸዋ ማተሚያ ድርጅት፣አዲስ ማተሚያ፣ በዕጓለ ማውታን እንዲሁም በተፈሪ መኮንን እና በተለያዩ ትምህርት ቤቶች አገልግለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካርዲናልን እና የአቡነ ዘካሪያስ ዮሃንስ ስዕሎችን በመስራትም አበርክቶ አድርገዋል።

ሰዓሊ ዮሀንስ ታደሰ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም በተወለዱ በ70 ዓመታቸው አርፈዋል።

የቀብር ስነስርዓታቸውም ለቡ በሚገኘው የካቶሊክ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዛሬው እለት ተፈፅሟል።

ሰዓሊ አቶ ዮሀንስ ባለትዳርና የ2 ሴት ልጆች አባት ነበሩ።

በትግስት ዘላለም
መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.