በኢትዮጵያ በውጭ አገራት ስራ ስምሪት ከተሰማሩ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ70 በላይ የሚሆኑን በኮሮና ቫይረስ ተጽዕኖ ምክንያት የስራ ፈቃዳቸውን እንደመለሱ የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህጋዊ ፍቃድ የተሰጣቸው ከ70 በላይ የሚሆኑ የውጭ ስራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የስራ ስምሪት በመቋረጡ ሳቢያ ስራቸውን ለማቋረጥ መገዳዳቸውን አስታውቋል።

ተቋሙ በዛሬው እለት በኮቪድ 19 ምክንያት ከመካከለኛው ምስራቅ ጎረቤት ሃገራት የተመለሱ ተጎጂ ዜጎችን ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ውይይት በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚህ የውይይት መድረክ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክተር ኤርጎኔ ተስፋዬን ጨምሮ የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት እና የኢጋድ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በሚኒስቴሩ የውጭ ሃገር ስራ ስምሪትና ዳሬክቶሬት ጀነራል አቶ ብርሃኑ አበራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት ከመካከላኛው ምስራቅ ሃገራትና ከጎረቤት ሃገራት ተጎድተው እንዲሁም በወረርሽኙ ምክንያት ተገደው ወደ ሃገራቸው የመጡ ዜጎችን እንዴት እናቋቁም፤የስራ ስምሪቱንስ ዝግ ወዳደረጉ ሃገራት በራቸውን እንዲከፍቱ ፤እንዲሁም ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎችን ለመግታት ከተቀባይ ሃገራት ጋር ስለተደረገ ድርድር እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

በገለፃውም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፤ በኤጀንሲዎች በዋናነት በስደት ተማላሾቹ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ተናግረዋል።

በሃገሪቱ እስካሁን ድረስ ከተለያዩ የውጪ ሃገራት ከ29 ሺ በላይ ከስደት ተማላሾች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

ከስደት ተመላሾችን ለመደግፍና መልሶ ለማቋቋም ባለመው በዚህ የውይይት መድረክ ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የድጋፍ ድርጅቶች የተገኘ ከ 217 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነትም በዛሬው እለት ተካሂዷል።

በየውልሰው ገዝሙ
መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *