የአዉሮፓ ህብረት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ሊጥል እንደሚችል ዝቷል፡፡

ህብረቱ ማዕቀብ እጥላለሁ ሲል የዛተዉ ቱርክ በምስራቃዊ የሜድትራኒያን የባህር ዳርቻ በኩል በግሪክ ላይ ያልተገባ ወታደራዊ ጫና እየፈጠረች ነዉ በሚል ነዉ፡፡

ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት እንዳለ ወደሚነገርለት ምስራቃዊ የሜድትራኒያን የባህር ዳርቻ ቱርክ መርከቦቿን መላኳን ተከትሎ ከግሪክ ጋር ዉጥረት ዉስጥ ገብተዋል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡርሱላ-ቮንዲር ሌይን እንዳሉት ዉጥረቱን እያባባሰችዉ ያለችዉ ቱርክ በመሆኗ ከዚህ ድርጊቷ እንድትቆጠብ ተነግሯታል፤ከድርጊቷ የማትታቀብ ከሆነ ግን ማዕቀብ ይጠብቃታል ብለዋል፡፡

አያይዘዉም ህብረቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር ከመሻት ዉጭ የተለየ ፍላጎት የለዉም ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.