ፕሬዝዳንት ትራምፕና ባለቤታቸዉ ለይቶ ማቆያ ገቡ፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ አማካሪ ሆፕ ሂክስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱና ባለቤታቸዉ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል፡፡

የ31 ዓመቷ የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ሆፕ ሂክስ ባሳለፍነዉ ማክሰኞና ረቡዕ ከፕሬዝዳንቱ ጋር እንደተገናኙ ሲገለጽ ለዛዉም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሳያደርጉ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ትራምፕ ትናንት ምሽት ላይ በቲዉተር ገጻቸዉ ላይ ባሰፈሩት መልክዕት አማካሪያቸዉ ያለ እረፍት ሲሰሩ መቆየታቸዉን ገልጸዉ በአሁኑ ሰዓት እርሳቸዉና ባለቤታቸዉ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አድርገዉ ዉጤቱን ራሳቸዉን አግልለዉ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ቢቢሲ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.