በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ዜጎች ቁጥጥር 700 ሚሊዮን በላይ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

በወቅቱ ከ35 ሚሊዮን በላይ የኮሮና ተጠቂ እንዳለ መረጃዎች ቢያሳዩም እውነተኛው የአለማችን የኮሮና ተጠቂዎች በመቶ ሚሊዮኖች ሊሆኑ እንደሚችሉ የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።

የተሻለውና ምርጡ ግምታችን ሊሆን የሚችለው ከአለም ህዝብ 10 በመቶው በኮሮና ተጠቅቷል የሚል ነው ብለዋል የአለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋ ስራዎች ሀላፊ ማይክ ርያን፡፡
የተጠቂው ቁጥር ከሀገር ሀገር እንዲሁም በከተማና በገጠር ይለያያል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አብዛኛው የአለም ህዝብ ግን አደጋ ውስጥ ሆኖ የመቆየቱን እውነታ አይቀይረውም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የኮቪድ 19 ተጠቂዎችና ሟቾች በአውሮፓ፣ በደቡብ ምስራቂ ኢስያ እና በምስራቅ ሜዲትራኒያን በአስደንጋጭ ሁኔታ ተስፋፍቷል በአፍሪካና በምዕራብ ፓስፊክ ግን የተሻለ ነው ብለዋል።

ወረርሽኙን የተመለከቱ ዝግመታዊ ለውጦች መኖራቸው እንደማይቀር ያነሱ ሲሆን አለም ግን ስርጭቱን ለመግታትና ህይወቶችን ለመታደግ መሳርያው እያላት መዝገሙ አይመረጥም ብለዋል፡፡

ወደፊታችን የሚወሰነውም እነዚህን መሳርያዎች እንዴት እንጠቀማቸው ብለን በጋራ በምንወስዳቸው ምርጫዎች ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የተመድ የጤና ወኪል አብዛኛው አለም አደጋ ውስጥ ነው ያለ ሲሆን የተባበረ እርምጃ ወረርሽኙ ላይ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ እስካሁን 35.2 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮና የተጠቁ ሲሆን ከ 1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ 24.5 ሚሊዮን ያህሉ ደግሞ አገግመዋል፡፡

በሔኖክ አስራት
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *