በደቡብ ክልል በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት 53 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መቋረጣቸውን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

እነዚህ ፕሮጀክቶች በክልል ደረጃ ከፍተኛ በጀት ተበጅቶላቸው እየተሰሩ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡

የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሃለፊ አቶ አስራት አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት አመታት በክልሉ በተፈጠሩ ግጭቶች የተነሳም ከ300 ሚሊየን ብር በላይ በሚገመት ንብረት መውደሙን ተናግረዋል፡፡

በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ኢንቨስተሮችም ክልሉ 90 ሚሊየን ብር የሚደርስ ካሳ መክፈሉንም አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡

በግጭቶች የተነሳ እንደ ሀገር የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ባለፉት ሁለት አመታት የተዳከመ እንደነበር የተናገሩት ሀላፊው የደቡብ ክልል በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አሁን በመሻሻል ላይ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ የክልሉ መንግስት የህዝቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄ በተገቢው መንገድ ሊመልስ በመቻሉ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ብሔር ተኮር የሆኑ ግጭቶች መልስ አለማግኝታቸው
አሁንም ቢሆንም ለክልሉ የኢንቨስትመት እድገት ማነቆ ናቸው ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.