ሞዛምቢክ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ሐሰተኛ ማስረጃ በሚሰጡ አካላት ላይ መርመራ ጀመረች።

በሞዛምቢክ መዲና ሞፑቱ ከተማ የኮሮና ነፃ መሆንን የሚረጋግጡ ሀሰተኛ ምስክር ወረቀቶች በጥቁር ገበያ በ7 ዶላር እየተሸጡ መሆናቸው ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ከዚህ ወንጀል ጀርባ ያሉ ግለሰቦች ላይ ምርመራ መጀመሯን ይፋ አአድርጋለች፡፡

ምርመራውን ለመጀመር ካነሳሱ ገፊ ምክንያቶች መካከል ከኮቪድ-19 የምርመራ ውጤት ነፃ መሆንን የሚያረጋግጡ ሰነዶች ሪፖርት መደረጋቸውን ተከትሎ መሆኑን የሞዛምቢክ የጤና ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡

እነዚህ የምስክር ወረቀቶች ገደብ የሌላቸው ከመሆናቸውም በላይ ቀጣይነትን ከሚያረጋግጡ የንግድ ሰነዶች ጋር እንዲያያዙ መደረጉ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

በማፑቶ ክልል የጤና ጉዳ ዳይሬክተር የሆኑት ዳንኤል ቼማኔ እንዳሉት ከኮቪድ-19 ነፃ መሆንን የሚያረጋግጡ የሀሰት ምስክር ወረቀቶች በጥቁር ገበያ በ7 የአሜሪካ ዶላር እየተሸጡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ህገ-ወጥ ተግባር በስተጀርባ ማን እንዳለ የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ቼማኔ ተናግረዋል፡፡
የሞዛምቢክ እና የአጎራባች ደቡብ አፍሪካ ተጓዦች ከጉዟቸው 72 ሰዓታት በፊት ከተወሰደ ናሙና ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፡፡

እነዚህ የኮሮና ቫይረስ ይለፍ ማስረጃዎችን ለማግኘት ዜጎች ሁሉንም አማራጮች እየተጠቀሙ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ሆኖም ምርመራዎቹ የሚከናወኑት በሀገሪቱ የግል ሆስፒታሎች ሲሆን ከ 41 እስከ 97 የሜሪካ ዶላር ወጪን መጠየቁ በብዙዎች ዘንድ ወድ መሆኑ ይገለፃል፡፡

ከዚህ ሁሉ ወደ ጥቁር ገበያው በማቅናት በ7 ዶላር እየሸመቱ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
በዚህ ድርጊት ውስጥ የተሰማሩ ግለሰቦችን ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሞዛምቢክ መንግስት መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.