ቻይና የኮቪድ 19 የክትባት ሂደት ላይ የደረሰችበትን ደረጃ የዓለም ጤና ድርጅት እውቅና እንዲሰጣት ጠየቀች፡፡

ቻይና ክትባቱን ለማግኘት የደረሰችበትን የምርምር ደረጃ የዓለም ጤና ድርጅት እውቅና እንዲሰጣት ጠይቃለች፡፡

በሃገሪቱ እየተከናወነ ያለው የኮቪድ 19 የክትባት ሂደትም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ድርድር ላይ መሆኗም ተነግሯል፡፡
በምዕራባዊ ፓስፊክ ክልል የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ለሮይተርስ እንዳሉት ቻይና እያሄደች ያለችውን የክትባት የምርምር ሂደትን በዓለም ጤና ደርጅት የክትባት ስም ዝርዝሮች ውስጥ እንዲካተቱ ቅድመ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ቻይና እስካሁን አራት የሙከራ ክትባቶችን አካሂዳለች ምንም እንኳን እስካሁን ውጤታማ ነው የሆነ ባይገኝም፡፡
ክትባቶቹም በ ፓኪስታን ፣ ኢንዶኔዥያ ፣ ብራዚል ፣ ሩሲያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባሉ አገሮች ውስጥ ቅድሚያ ተሰቷቸዋል፡፡

የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ ባለፈው ወር በቻይናም ሆነ ሩሲያ ለሚካሄዱ የኮቪድ 19 የክትባት ውጤቶችን በሃገራቸው ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ እሰጣለሁ ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.