ኢትዮጵያ ያሏት ስፔሻላይዝድ የአይን ሐኪሞች ዘጠኝ ብቻ መሆናቸውን ያውቃሉ

ከሰሃራ በረሃ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን አይነ ስውራን ያሉ ሲሆን ከ17 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሙ ጽኑ የዓይን ህመምተኞች መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያስረዳል።

ኢትዮጵያም ከፍተኛ የአይነ ስውራን እና የአይን ህመም ተጠቂዎች ካላቸው አገራት መካከል ተጠቃሽ ናት።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የአይን ህክምና እየሰጡ የሚገኙ ሀኪሞች ከ160 የማይበልጡ ሲሆን ስፔሻላይዝድ የአይን ሐኪሞች ቁጥር ደግሞ 9 ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአይን ህክምና ትምህርት ክፍል እና የአይን ህክምና ማህበር ሀላፊ ዶ/ር ሳዲቅ ታጁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በኢትዮጵያ በአይን ህክምና አሰጣጥ ላይ ያለው ትልቁ ችግር የባለሙያዎች እጥረት ነው ብለዋል፡፡

ይህም በዓለም አቅፍ የጤና ድርጅት መመዘኛ አንጻር ሲታይ እጅግ ያነሰ ነው እንደሆነ ነው ዶ/ር ሳዲቅ የተናገሩት፡፡

በሀገሪቱ የአይን ንቅለ ተከላ የሚፈልጉ ዜጎች በርካታ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በሚቀጥሉት አስርት አመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአይን ንቅለ ተከለ አገልግሎት ሊሰጥ እንደሆነ ዶ/ር ሳዲቅ ተናግረዋል፡፡

በየአመቱ በዘርፉ የሚመረቁ ባለሙያዎች ቁጥርም ሲታይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ተብሏል፡፡

ህክምናው ከሚፈልገው ህዝብ አንጻር ሲመዘንም እጅግ የተመጣጠነ እንዳልሆነ እና በመላው ሀገሪቱም ተደራሽ እንዳልሆነ ነው የተገለጸው፡፡

በሀገሪቱ ከዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል በተጨማሪ የአይን ህክምና እየተሰጠ የሚገኝው በመቀሌ ፣ጎንደር፣ ጅማ እና በሀዋሳ ከተሞች ብቻ ነው፡፡

በጋምቤላ በአፋር እንዲሁም በቤንሻንጉል የአይን ህክምና የማይሰጥ ሲሆን ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የባለሙያዎች እጥረት ነው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት 14 አመታት በተደረገ ጥረት የአይን ንቅለ ተከላ የተደረገው ለ2 ሺህ 400 ዜጎች ብቻ ነው ተብሏል፡፡

ይህ በመሆኑም ሀገሪቷ በሰው ሀብት ልማቱ ላይ በሰፊው መስራት አለባት ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *