ደቡብ ሱዳን 14 አዳዲስ የነዳጅ ፕሮጀክቶችን ልትገነባ መሆኑን አስታወቀች።

ደቡብ ሱዳን ወደ ጦርነት ከመግባቷ በፊት በቀን 300 ሺህ በርሜል ታመርት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በቀን 165 ሺህ አሽቆልቁሏል።

የሃገሪቱ የፔትሮሊየም ሚኒስትር አዎው ዳንኤል ቹናንግ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም የነዳጅ ምርቱ በቀን ሲመረት ከነበረው 130 ሺህ በርሜል ወደ 115 ሺህ አሻቅቧል።

በሃገሪቱ በነዳጅ ምርት ላይ እየገጠመን ያለውን ችግር ለመግታትና ተጨማሪ የነዳጅ ፋብሪካዎችን ለመትከል ቴክኒካዊው ስልቶችን እየነደፍን ነን ብለዋል የሃገሪቱ የፔትሮሊየም ዳይሬክተሯ።

በሃገሪቱ ከሰባት ዓመታት በላይ የዘለቀው ግጭት ከመከሰቱ በፊት በቀን ወደ 300 ሺህ በርሜል የነዳጅ ምርት በቀን ይቀርብ እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል።

ወደ ቀደመ የምርት ሂደት መመለስ ለእኛ ቀላል አይደለም ፣ በጂኦሎጂካል ተግዳሮቶች የተነሳ ያንን ማድረግ አንችልም እናም በተመሳሳይ ጊዜ የነዳጅ ክምችት ውስን በመሆኑ በምርቱ ላይ ማሽቆልቆል እንዳለ እንገነዘባለን ብለዋል ዳይሬክተሯ፡፡

ሰሞኑን በነዳጅ አምራቹ የላይኛው ናይል ክልል ውስጥ የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅም በነዳጅ እርሻዎች ምርት ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ሲጂቲኤን ዘግቧል።

በየውልሰው ገዝሙ
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *