ጅቡቲ ድንበሯን ባለመክፋቷ ምክንያት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር መቸገሩን የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።

ባለፈው ዓመት 17 ሚሊየን ቶን ያህል ግብዓቶችን ወደ ሃገር ውስጥ ሲያጓጓዝ ሶስት ሚሊየን ቶን ጭነት ደግሞ ወደ ጅቡቲ አሻግሯል፡፡

የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጥላሁን ሳርቃ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከፍተኛ የህዝብ ምልልስ ያለው በድሬደዋ እና በጂቡቲ መካከል ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ጂቡቲ ድንበሯን ዝግ በማድረጓ ስራው ተቋርጧል፡፡

በእኛ በኩል ስራውን ለመጀመር ፍላጎት ቢኖርም ከጂቡቲ በኩል ግን ይህን የተመለከተ ፍንጭ አላገኘንም ብለዋል ኢንጂነር ጥላሁን፡፡

አክሲዮን ማህበሩ በዋናነት ተግባሩ ከፍተኛ የገቢ ዕቃዎችን ማመላለስ እንደሆነ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ባለፈው ዓመት ብቻ 17 ሚሊየን ቶን የገቢ ዕቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ከሃገር ወደ ውጪ ደግሞ ሶስት ሚሊየን ቶን ጭነት አጓጉዟል፡፡

ይህም ከፍተኛ የንግድ ጉድለት እንዳለ የሚጠቁም ስለመሆኑ ያብራራሉ፡፡
ከ17 ሚሊየን ቶን ውስጥ 50 በመቶውን የሚይዘው የኮንቴይነር ዕቃዎች ናቸው፡፡

በመቀጠል ነዳጅ እና የቅባት ጭነት ሁለተኛ ስፍራን ይይዛል፡፡ ባለፈው ዓመት ሃገሪቱ 4 ሚሊየን ሜክትሪክ ቶን ነዳጅ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ አስገብታለች፡፡

በሶስተኝነት 4 ሚሊየን ቶን ስንዴና ማዳበሪያ ተጓጉዟል፡፡ አንድ ሚሊየን ቶን የኮንስትራክሽን ቁሳቁሶች በዋናነት ብረታብረት ወደ ሃገር ውስጥ ገብቷል፡፡

ሌሎች ዕቃዎች ቀሪውን ስፍራ እንደሚይዙ ሰምተናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.